بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمـَنِ الرَّحِيمِ


ق ۚ وَالْقُرْآنِ الْمَجِيدِ

ቃፍ በተከበረው ቁርአን እምላለሁ፤ በሙሐመድ አላመኑም።

بَلْ عَجِبُوا أَن جَاءَهُم مُّنذِرٌ مِّنْهُمْ فَقَالَ الْكَافِرُونَ هَـٰذَا شَيْءٌ عَجِيبٌ

ግና ከውስጣቸው አስፈራሪ ስለመጣላቸው ተደነቁ፤ በመሆኑም ከሐዲዎቹ ፦ ይህ አስደናቂ ነገር ነው፣ አሉ።

أَإِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا ۖ ذَ‌ٰلِكَ رَجْعٌ بَعِيدٌ

በሞትንና አፈር ሆንን በኋላልንቀሰቀስ? ይህ ከእውነታ እጅግ የራቀ መመለስ ነው።አሉም።

قَدْ عَلِمْنَا مَا تَنقُصُ الْأَرْضُ مِنْهُمْ ۖ وَعِندَنَا كِتَابٌ حَفِيظٌ

ምድር ከነርሱ ከአካላቸው የምታጐድለውን አውቀናል።ከኛ ዘንድ መረጃዎችን ሁሉ ያካተተጠባቂ መዝገብ አለ።

بَلْ كَذَّبُوا بِالْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُمْ فَهُمْ فِي أَمْرٍ مَّرِيجٍ

እውነትን በመጣላቸው ጊዜ አስተባባሉ።እነርሱ ውዥንብር ውስጥ ናቸውና።

أَفَلَمْ يَنظُرُوا إِلَى السَّمَاءِ فَوْقَهُمْ كَيْفَ بَنَيْنَاهَا وَزَيَّنَّاهَا وَمَا لَهَا مِن فُرُوجٍ

ከበላያቸው ያለውን ሰማይ አንዳች ሽንቁር የሌለው አድርገን እንዴት እንደገነባነውና እንዳስዋብነው አያዩምን?

وَالْأَرْضَ مَدَدْنَاهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍ بَهِيجٍ

ምድርንም ዘረጋናት።ከበላይዋም ጋራዎችን አቆምን።ከውስጧም አስደሳች የሆኑ የእፅዋትአይነቶችን ሁሉ አበቀልን።

تَبْصِرَةً وَذِكْرَىٰ لِكُلِّ عَبْدٍ مُّنِيبٍ

ወደ አላህተመላሾች ለሆኑ አገልጋዮች ሁሉጥበባችንንለማሳየት የላቀ ችሎታችንንለማስገንዘብይህን ፈፀምን።

وَنَزَّلْنَا مِنَ السَّمَاءِ مَاءً مُّبَارَكًا فَأَنبَتْنَا بِهِ جَنَّاتٍ وَحَبَّ الْحَصِيدِ

ከሰማይም የተባረከ ውሃን አወረድን።በርሱም አትክልቶችንና የሚታጨድንአዝመራአበቀልን።

وَالنَّخْلَ بَاسِقَاتٍ لَّهَا طَلْعٌ نَّضِيدٌ

የተነባበሩ እምቡጦችን ያሏቸውን የዘንባባ ዛፎችምአበቀልን

رِّزْقًا لِّلْعِبَادِ ۖ وَأَحْيَيْنَا بِهِ بَلْدَةً مَّيْتًا ۚ كَذَ‌ٰلِكَ الْخُرُوجُ

ለሰው ልጆች ሲሳይ ይሆኑ ዘንድ።በርሱም የሞተችን መሬት ሕያው አደረግን።ከሞትመነሳትም እንደዚሁ ነው።

كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ وَأَصْحَابُ الرَّسِّ وَثَمُودُ

ከነርሱ በፊት የኑሕ ሕዝቦች የአርረስ ሰዎችና ሠሙዶችየመጭውን ዓለም ሕልውናአስተባብለዋል።

وَعَادٌ وَفِرْعَوْنُ وَإِخْوَانُ لُوطٍ

ነገደዓድም ፊርዐውንም የሉጥ ወንድሞችም

وَأَصْحَابُ الْأَيْكَةِ وَقَوْمُ تُبَّعٍ ۚ كُلٌّ كَذَّبَ الرُّسُلَ فَحَقَّ وَعِيدِ

የአይከህ ሰዎችና የቱብባዕ ሕዝቦችም እንዲሁ።ሁሉም መልዕክተኞቼን አስተባባሉ።በመሆኑም ዛቻዬ ተፈፀመባቸው።

أَفَعَيِينَا بِالْخَلْقِ الْأَوَّلِ ۚ بَلْ هُمْ فِي لَبْسٍ مِّنْ خَلْقٍ جَدِيدٍ

የመጀመሪያው ፈጠራ ተስኖን ነበርን?ይልቅ እነርሱ ዳግም ፈጠራውን በእጀጉ የጠራጠራሉ።

وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ وَنَعْلَمُ مَا تُوَسْوِسُ بِهِ نَفْسُهُ ۖ وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ الْوَرِيدِ

የሰውን ልጅ የፈጠርነው እኛው ነን።ነፍሱ የምትጐተጉተውን እንኳ ሳይቀርጠንቅቀን እናውቃለን።እኛ ለርሱ ከደም ጋን ጅማቱ ይበልጥ የቀረብን ነን

إِذْ يَتَلَقَّى الْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ قَعِيدٌ

ሁለቱ ቃል ተቀባይመላእክትበቀኙም በግራውም ተቀምጠው ቃሉን በሚቀበሉት ወቅትየሚሆነውን አስታውስ።

مَّا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ

ከቃል አንድንም አይናገርም ከርሱ ዘንድቃሉን ለመመዝገብዝግጁ የሆኑ መላእክት ያሉ ቢሆን እንጅ።

وَجَاءَتْ سَكْرَةُ الْمَوْتِ بِالْحَقِّ ۖ ذَ‌ٰلِكَ مَا كُنتَ مِنْهُ تَحِيدُ

ጣዕረ ሞት በእርግጥም ይመጣበታል።ይህ ትሸሸው የነበረውሞትነው።ይባላልም።

وَنُفِخَ فِي الصُّورِ ۚ ذَ‌ٰلِكَ يَوْمُ الْوَعِيدِ

በቀንዱም ውስጥ ይነፋል።ያ ቀን የዛቻውመፈፀሚያቀን ይሆናል።

وَجَاءَتْ كُلُّ نَفْسٍ مَّعَهَا سَائِقٌ وَشَهِيدٌ

ነፍስም ሁሉ ከእርሷ ጋር ነጂና መስካሪ ያለባት ኾና ትመጣለች፡፡

لَّقَدْ كُنتَ فِي غَفْلَةٍ مِّنْ هَـٰذَا فَكَشَفْنَا عَنكَ غِطَاءَكَ فَبَصَرُكَ الْيَوْمَ حَدِيدٌ

«ከዚህ ነገር በእርግጥ በዝንጋቴ ውስጥ ነበርክ፡፡ ሺፋንህንም ካንተ ላይ ገለጥንልህ፡፡ ስለዚህ ዛሬ ዓይንህ ስለታም ነው» ይባላል፡፡

وَقَالَ قَرِينُهُ هَـٰذَا مَا لَدَيَّ عَتِيدٌ

ቁራኛውም መልአክ «ይህ ያ እኔ ዘንድ ያለው ቀራቢ ነው» ይላል፡፡

أَلْقِيَا فِي جَهَنَّمَ كُلَّ كَفَّارٍ عَنِيدٍ

«ሞገደኛ ከሓዲን ሁሉ በገሀነም ውስጥ ጣሉ፡፡»

مَّنَّاعٍ لِّلْخَيْرِ مُعْتَدٍ مُّرِيبٍ

«ለበጎ ሥራ ከልካይ፣ በዳይ፣ ተጠራጣሪ የኾነን ሁሉ፤» ጣሉ፡፡

الَّذِي جَعَلَ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ فَأَلْقِيَاهُ فِي الْعَذَابِ الشَّدِيدِ

«ያንን ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ ያደረገውን በብርቱ ቅጣት ውስጥ ጣሉት፤» ይባላል፡፡

 ۞ قَالَ قَرِينُهُ رَبَّنَا مَا أَطْغَيْتُهُ وَلَـٰكِن كَانَ فِي ضَلَالٍ بَعِيدٍ

ቁራኛው ሰይጣን «ጌታችን ሆይ! እኔ አላሳሳትኩትም፡፡ ግን ራሱ በሩቅ ስሕተት ውስጥ ነበር» ይላል፡፡

قَالَ لَا تَخْتَصِمُوا لَدَيَّ وَقَدْ قَدَّمْتُ إِلَيْكُم بِالْوَعِيدِ

አላህ «ወደእናንተ ዛቻን በእርግጥ ያስቀደምኩ ስኾን እኔ ዘንድ አትጨቃጨቁ» ይላቸዋል፡፡

مَا يُبَدَّلُ الْقَوْلُ لَدَيَّ وَمَا أَنَا بِظَلَّامٍ لِّلْعَبِيدِ

«ቃሉ እኔ ዘንድ አይለወጥም፡፡ እኔም ለባሮቼ ፈጽሞ በዳይ አይደለሁም» ይላቸዋል፡፡

يَوْمَ نَقُولُ لِجَهَنَّمَ هَلِ امْتَلَأْتِ وَتَقُولُ هَلْ مِن مَّزِيدٍ

ለገሀነም «ሞላሽን? የምንልበትንና ጭማሪ አለን? የምትልበትን ቀን» አስጠንቅቃቸው፡፡

وَأُزْلِفَتِ الْجَنَّةُ لِلْمُتَّقِينَ غَيْرَ بَعِيدٍ

ገነትም አላህን ለፈሩት እሩቅ ባልኾነ ስፍራ ትቅቀረባለች፡፡

هَـٰذَا مَا تُوعَدُونَ لِكُلِّ أَوَّابٍ حَفِيظٍ

«ይህ ወደ አላህ ተመላሽና ሕግጋቱን ጠባቂ ለኾነ ሁሉ የተቀጠራችሁት ነው» ይባላሉ፡፡

مَّنْ خَشِيَ الرَّحْمَـٰنَ بِالْغَيْبِ وَجَاءَ بِقَلْبٍ مُّنِيبٍ

«አልረሕማንን በሩቁ ኾኖ ለፈራና በንጹሕ ልብ ለመጣ» ትቅቀረባለች፡፡

ادْخُلُوهَا بِسَلَامٍ ۖ ذَ‌ٰلِكَ يَوْمُ الْخُلُودِ

«በሰላም ግቧት ይህ የመዘውተሪያ ቀን ነው» ይባላሉ፡፡

لَهُم مَّا يَشَاءُونَ فِيهَا وَلَدَيْنَا مَزِيدٌ

ለነርሱ በውስጧ ሲኾኑ የሚሹት ሁሉ አልላቸው፡፡ እኛም ዘንድ ጭማሪ አልለ፡፡

وَكَمْ أَهْلَكْنَا قَبْلَهُم مِّن قَرْنٍ هُمْ أَشَدُّ مِنْهُم بَطْشًا فَنَقَّبُوا فِي الْبِلَادِ هَلْ مِن مَّحِيصٍ

ከእነርሱም ከቁረይሾች በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን እነርሱ በኀያልነት ከእነርሱ ይበልጥ የበረቱ የኾኑትን ማምለጫ ፍለጋ በየአገሮቹም የመረመሩትን አጥፍተናል፡፡ ማምለጫ አለን?

إِنَّ فِي ذَ‌ٰلِكَ لَذِكْرَىٰ لِمَن كَانَ لَهُ قَلْبٌ أَوْ أَلْقَى السَّمْعَ وَهُوَ شَهِيدٌ

በዚህ ውሰጥ ለእርሱ ልብ ላለው ወይም እርሱ በልቡ የተጣደ ኾኖ ወደሚነበብለት ጆሮውን ለጣለ ሰው ግሳጼ አለበት፡፡

وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ

ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡

فَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ وَقَبْلَ الْغُرُوبِ

በሚሉትም ላይ ታገሥ፤ ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው፡፡

وَمِنَ اللَّيْلِ فَسَبِّحْهُ وَأَدْبَارَ السُّجُودِ

ከሌሊቱም አወድሰው ከስግደቶችም በኋላዎች አወድሰው፡፡

وَاسْتَمِعْ يَوْمَ يُنَادِ الْمُنَادِ مِن مَّكَانٍ قَرِيبٍ

የሚነገርህን አዳምጥም፡፡ ጠሪው ከቅርብ ስፍራ በሚጠራበት ቀን ከመቃብራቸው ይወጣሉ፡፡

يَوْمَ يَسْمَعُونَ الصَّيْحَةَ بِالْحَقِّ ۚ ذَ‌ٰلِكَ يَوْمُ الْخُرُوجِ

ጩኸቲቱን በእውነት የሚሰሙበት ቀን ያ ከመቃብር የመውጫው ቀን ነው፡፡

إِنَّا نَحْنُ نُحْيِي وَنُمِيتُ وَإِلَيْنَا الْمَصِيرُ

እኛ እኛው ሕያው እናደርጋለን፡፡ እንገድላለንም፡፡ መመለሻም ወደእኛ ብቻ ነው፡፡

يَوْمَ تَشَقَّقُ الْأَرْضُ عَنْهُمْ سِرَاعًا ۚ ذَ‌ٰلِكَ حَشْرٌ عَلَيْنَا يَسِيرٌ

የሚፈጥኑ ኾነው ምድር ከእነርሱ ላይ የምትሰነጣጠቅበት ቀን የመውጫው ቀን ነው፡፡ ይህ በእኛ ላይ ገር የኾነ መሰብሰብ ነው፡፡

نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَقُولُونَ ۖ وَمَا أَنتَ عَلَيْهِم بِجَبَّارٍ ۖ فَذَكِّرْ بِالْقُرْآنِ مَن يَخَافُ وَعِيدِ

እኛ የሚሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነን፡፡ አንተም በእነርሱ ላይ አስገዳጅ አይደለህም፡፡ ስለዚህ ዛቻየን የሚፈራን ሰው በቁርኣን አስታውስ፡፡

ቃሪዕ ይምረጡ