بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمـَنِ الرَّحِيمِ


اقْتَرَبَتِ السَّاعَةُ وَانشَقَّ الْقَمَرُ

ስዓቲቱ የትንሣኤ ቀን ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፤

وَإِن يَرَوْا آيَةً يُعْرِضُوا وَيَقُولُوا سِحْرٌ مُّسْتَمِرٌّ

ታምርንም ቢያዩ ከአምነት ይዞራሉ ይህ ዘውታሪ ደግመት ነውም ይላሉ

وَكَذَّبُوا وَاتَّبَعُوا أَهْوَاءَهُمْ ۚ وَكُلُّ أَمْرٍ مُّسْتَقِرٌّ

አስተባበሉም፤ ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ፤ ነገርም ሁሉ ወሰን አለው፤ ረጊ ነው::

وَلَقَدْ جَاءَهُم مِّنَ الْأَنبَاءِ مَا فِيهِ مُزْدَجَرٌ

ከዜናዎችም በርሱ ውስጥ መገሠጥ ያለበት ነገር በእርግጥ መታላቸው::

حِكْمَةٌ بَالِغَةٌ ۖ فَمَا تُغْنِ النُّذُرُ

ሙሉ የሆነች ጥበብ መጣቻቸው ግን አስፈራሪዎቹ አይብቃቁም::

فَتَوَلَّ عَنْهُمْ ۘ يَوْمَ يَدْعُ الدَّاعِ إِلَىٰ شَيْءٍ نُّكُرٍ

ከነርሱም ዙር፡ ጠሪው መልአክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ።

خُشَّعًا أَبْصَارُهُمْ يَخْرُجُونَ مِنَ الْأَجْدَاثِ كَأَنَّهُمْ جَرَادٌ مُّنتَشِرٌ

ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ሆነው ፍፁም የተበተነ አንበጣ መስለው ከመቃብሮቹ ይወሉ::

مُّهْطِعِينَ إِلَى الدَّاعِ ۖ يَقُولُ الْكَافِرُونَ هَـٰذَا يَوْمٌ عَسِرٌ

ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎች ቸካዮች ሆነው ይወጣሉ ከሐዲዎች ያን ጊዜ ምን ይላሉ? ይህ ብርቱ ቀን ነው ይላሉ፤

 ۞ كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ فَكَذَّبُوا عَبْدَنَا وَقَالُوا مَجْنُونٌ وَازْدُجِرَ

ከነሱ በፊት የኑሕ ነገድ አስተባበለች። ባሪያችንንም ኑሕን አስተባበሉ፤ እብድ ነውም አሉ፤ ተገለመጠም።

فَدَعَا رَبَّهُ أَنِّي مَغْلُوبٌ فَانتَصِرْ

ጌታውንም እኔ የተሽነፍኩ ነኝና እርዳኝ ሲል ጠራ።

فَفَتَحْنَا أَبْوَابَ السَّمَاءِ بِمَاءٍ مُّنْهَمِرٍ

ወዲያዉም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን፡

وَفَجَّرْنَا الْأَرْضَ عُيُونًا فَالْتَقَى الْمَاءُ عَلَىٰ أَمْرٍ قَدْ قُدِرَ

የምድርንም ምንጮች አፈነዳን፤ ውሃውም የስማይና የምድሩ በእርግጥ የተወሰነ ሁኔታ ላይ ተገናኘ::

وَحَمَلْنَاهُ عَلَىٰ ذَاتِ أَلْوَاحٍ وَدُسُرٍ

ባለ ሳንቃዎችና ባለ ሚስማሮች በሆነችም ታንኳ ላይ ጫነው፤

تَجْرِي بِأَعْيُنِنَا جَزَاءً لِّمَن كَانَ كُفِرَ

በጥበቃችን ስር ሆና ተንሻለላለች። ተክዶ ለነበረው ስው ምንዳ ይሕንን ሠራን።

وَلَقَد تَّرَكْنَاهَا آيَةً فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ

ታምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት፤ ከተገሣጭም አለልን?

فَكَيْفَ كَانَ عَذَابِي وَنُذُرِ

ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ?

وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ

ቁርአንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው ተገንዛቢም አልለን?

كَذَّبَتْ عَادٌ فَكَيْفَ كَانَ عَذَابِي وَنُذُرِ

ዓድ አስተባበለች ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ!

إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ رِيحًا صَرْصَرًا فِي يَوْمِ نَحْسٍ مُّسْتَمِرٍّ

እኛ በነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በኾነ ቀን በቫይል የምትንሻሻ ነፋስን ላክንባቸው::

تَنزِعُ النَّاسَ كَأَنَّهُمْ أَعْجَازُ نَخْلٍ مُّنقَعِرٍ

ስዎችን ልክ ከሥሮቻቸው የተጐለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው ከተደበቁበት ትነቅላቸዋለች።

ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ?

ቁርአንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው ተገሣጭም አለን?

كَذَّبَتْ ثَمُودُ بِالنُّذُرِ

ሠሙድ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች።

فَقَالُوا أَبَشَرًا مِّنَّا وَاحِدًا نَّتَّبِعُهُ إِنَّا إِذًا لَّفِي ضَلَالٍ وَسُعُرٍ

ከኛ የሆነን አንድን ስው እንከተለዋለን? እኛ ያን ጊዜ በስሕተትና በዕብደት ውስጥ ነን አሉ::

أَأُلْقِيَ الذِّكْرُ عَلَيْهِ مِن بَيْنِنَا بَلْ هُوَ كَذَّابٌ أَشِرٌ

ከኛ መካከል በርሱ ላይ ብቻ ማስገንዘቢያ ራእይ ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ዉሽታም ኩሩ ነው አሉ።

سَيَعْلَمُونَ غَدًا مَّنِ الْكَذَّابُ الْأَشِرُ

ዉሽታሙ፤ ኩሩው ማን እንደሆነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ::

إِنَّا مُرْسِلُو النَّاقَةِ فِتْنَةً لَّهُمْ فَارْتَقِبْهُمْ وَاصْطَبِرْ

እኛ ሴት ግመልን ለነርሱ መፈተኛ ትሆን ዘንድ ላኪዎች ነን፤ ተጠባበቃቸውም፤ ታገሥም::

وَنَبِّئْهُمْ أَنَّ الْمَاءَ قِسْمَةٌ بَيْنَهُمْ ۖ كُلُّ شِرْبٍ مُّحْتَضَرٌ

ውሃውም በመካከላቸው የተከፈለ መሆኑን ንገራቸው፤ ከውሃ የሆነ ፋንታ ሁሉ ተረኞቹ የሚጣዱት ነው::

فَنَادَوْا صَاحِبَهُمْ فَتَعَاطَىٰ فَعَقَرَ

ጓደኛቸውንም ጠሩ፤ ወዲያውም ስይፍን ተቀበለ፤ ወጋትም ::

ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ?

إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ صَيْحَةً وَاحِدَةً فَكَانُوا كَهَشِيمِ الْمُحْتَظِرِ

እኛ፤ በነሱ ላይ አንዲትን ጩኸት ላክንባቸው፤ ወዲያውም ከበረት አጣሪ አጥር እንደ ተስባበረ ርግጋፌ ሆኑ::

ቁርአንንም ለመገንዘብ አገራነው፤ ተገሣጭም አለን?

كَذَّبَتْ قَوْمُ لُوطٍ بِالنُّذُرِ

የሉጥ ሕዝብ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች::

إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ حَاصِبًا إِلَّا آلَ لُوطٍ ۖ نَّجَّيْنَاهُم بِسَحَرٍ

እኛ በነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋሰን ላክን። የሉጥ ቤተስቦች ብቻ ሲቀሩ እነሱንስ በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው፤

نِّعْمَةً مِّنْ عِندِنَا ۚ كَذَ‌ٰلِكَ نَجْزِي مَن شَكَرَ

ከኛ በሆነ ጸጋ አዳንናቸው እንደዚሁ ያመስገነን ስው እንመነዳለን ::

وَلَقَدْ أَنذَرَهُم بَطْشَتَنَا فَتَمَارَوْا بِالنُّذُرِ

ብርቱይቱን አያያዛችንንም በእርግጥ አስጠነቀቃቸው፤ በማስጠንቀቂያዎቹም ተከራከሩ::

وَلَقَدْ رَاوَدُوهُ عَن ضَيْفِهِ فَطَمَسْنَا أَعْيُنَهُمْ فَذُوقُوا عَذَابِي وَنُذُرِ

ከእንግዶቹም እንዲያስመቻቸው ደጋግመው ፈለጉት ወዲያዉም ዓይኖቻቸውን አበስን፤ ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼንም ቅመሱ አልናቸው::

وَلَقَدْ صَبَّحَهُم بُكْرَةً عَذَابٌ مُّسْتَقِرٌّ

በማለዳም ዘውታሪ የሆነ ቅጣት በእርግጥ ማለደባቸው::

فَذُوقُوا عَذَابِي وَنُذُرِ

ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎችንም ቅመሱ ተባሉ።

ቁራአንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፤ ተገሳጭም አልለን ?

وَلَقَدْ جَاءَ آلَ فِرْعَوْنَ النُّذُرُ

የፈርዖንንም ቤተስቦች ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጡዋቸው፤

كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا كُلِّهَا فَأَخَذْنَاهُمْ أَخْذَ عَزِيزٍ مُّقْتَدِرٍ

በታምራቶቻችን በሁሏም አሰተባበሉ፤ የብርቱ ቻይንም አያያዝ ያዝናቸው::

أَكُفَّارُكُمْ خَيْرٌ مِّنْ أُولَـٰئِكُمْ أَمْ لَكُم بَرَاءَةٌ فِي الزُّبُرِ

ከሐዲዎቻችሁ ከነዚሃችሁ በላጮች ናቸውን? ወይስ ለናንተ በመዽሐፎች ውስጥ የተነገረ ነጣነት አላችሁን?

أَمْ يَقُولُونَ نَحْنُ جَمِيعٌ مُّنتَصِرٌ

ወይስ እኛ የተረዳን ክምቹዎች ነን ይላሉን?

سَيُهْزَمُ الْجَمْعُ وَيُوَلُّونَ الدُّبُرَ

ከምቹዎቹ በእርግጥ ድል ይመታሉ፤ ጀርባዎችንም ያዞራሉ::

بَلِ السَّاعَةُ مَوْعِدُهُمْ وَالسَّاعَةُ أَدْهَىٰ وَأَمَرُّ

ይልቁንም ስዓቲቱ ትንሣኤቀጠሮዋቸው ናት፤ ስዓቲቱም በጣም የከበደችና የመረረች ናት፤

إِنَّ الْمُجْرِمِينَ فِي ضَلَالٍ وَسُعُرٍ

አመጠኞች በስሕተትና በእሳቶች ውስጥ ናቸው፤

يَوْمَ يُسْحَبُونَ فِي النَّارِ عَلَىٰ وُجُوهِهِمْ ذُوقُوا مَسَّ سَقَرَ

በእሳት ውስጥ በፊቶቻቸው በሚጎተቱበት ቀን የስቀርን 1 መንካት ቅመሱ ይባላሉ

إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ

እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፤

وَمَا أَمْرُنَا إِلَّا وَاحِدَةٌ كَلَمْحٍ بِالْبَصَرِ

ትእዛዛችንም እንደ ዓይን ቅዽበት አንዲት ቃል እንጅ ሌላ አይደለም፤

وَلَقَدْ أَهْلَكْنَا أَشْيَاعَكُمْ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ

ብጤዎቻችሁንም በእርግጥ አጠፋን ተገሣጭም አልለን?፤

وَكُلُّ شَيْءٍ فَعَلُوهُ فِي الزُّبُرِ

የሠሩትንም ነገር ሁሉ በመጽሐፎች ዉስጥ ነው፤

وَكُلُّ صَغِيرٍ وَكَبِيرٍ مُّسْتَطَرٌ

ትንሹም ትልቁም ሁሉ የተጻፍ ነው፤

إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَنَهَرٍ

አላህን ፈሪዎች በአትክልቶችና በወንዞች ዉስጥ ናቸው፤

فِي مَقْعَدِ صِدْقٍ عِندَ مَلِيكٍ مُّقْتَدِرٍ

እነሱም ውድቅ ቃልና መወንጀል በሌለበት በውነት መቀመጫ ዉስጥ ቻይ እሆነው ንጉስ ዘንድ ናቸው::

ቃሪዕ ይምረጡ