بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمـَنِ الرَّحِيمِ


قَدْ سَمِعَ اللَّهُ قَوْلَ الَّتِي تُجَادِلُكَ فِي زَوْجِهَا وَتَشْتَكِي إِلَى اللَّهِ وَاللَّهُ يَسْمَعُ تَحَاوُرَكُمَا ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ

አላህ የዚያችን በባልዋ ነገር የምትከራከርህንና ወደአላህ የምታስሙተውን ሴት ቃል በእርግጥ ስማ አላህም። በንግግር መመላለሳችሁን ይስማል። አላህ ስሚ ተመልካች ነውና።

الَّذِينَ يُظَاهِرُونَ مِنكُم مِّن نِّسَائِهِم مَّا هُنَّ أُمَّهَاتِهِمْ ۖ إِنْ أُمَّهَاتُهُمْ إِلَّا اللَّائِي وَلَدْنَهُمْ ۚ وَإِنَّهُمْ لَيَقُولُونَ مُنكَرًا مِّنَ الْقَوْلِ وَزُورًا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ لَعَفُوٌّ غَفُورٌ

እነዚያ ከናንተ ውስጥ ከሚስቶቻቸው እንደናቶቻቻን ጀርባዎች ይሁኑብን በማለት የሚምሉ እነሱ እናቶቻቸው አይደሉም፤ እናቶቻቸው አሊያ የወለዱዋቸው ብቻ ናቸው። እነርሱም በዚህ ቃል ከንግግር የተጠላንና ውሸትን በእርግጥ ይናገራሉ፤ አላህም ለሚጸጸት ይቅርባይ መሃሪ ነው።

وَالَّذِينَ يُظَاهِرُونَ مِن نِّسَائِهِمْ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا قَالُوا فَتَحْرِيرُ رَقَبَةٍ مِّن قَبْلِ أَن يَتَمَاسَّا ۚ ذَ‌ٰلِكُمْ تُوعَظُونَ بِهِ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ

እነዚያም ከሚስቶቻቸው እንደ እናቶቻችን፣ ጀርባዎች ኽኑብን በማለት የሚምሉ፣ ከዚያም ወደ ተናገሩት የሚመለሱ ሳይነካኩ በፊት ጫንቃን ነጻ ማውጣት በነሱ ላይ አለባቸው። ይሃችሁ በርሱ ትገሠጹበታላችሁ፤ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።

فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ شَهْرَيْنِ مُتَتَابِعَيْنِ مِن قَبْلِ أَن يَتَمَاسَّا ۖ فَمَن لَّمْ يَسْتَطِعْ فَإِطْعَامُ سِتِّينَ مِسْكِينًا ۚ ذَ‌ٰلِكَ لِتُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ۚ وَتِلْكَ حُدُودُ اللَّهِ ۗ وَلِلْكَافِرِينَ عَذَابٌ أَلِيمٌ

ያላገኘም ሰው ከመነካካታቸው በፊት ሁለት የተከታተሉ ወሮችን መጾም አለበት ያልቻለም ሰው ስድሳ ድሆችን ማብላት አለበት፤ ይህ በአላህና በመልክተኛው እንድታምኑ ነው። ይህችም የአላህ ህግጋት ናት ለካሃዲዎችም አሳማሚ ቅጣት አልላቸው።

إِنَّ الَّذِينَ يُحَادُّونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ كُبِتُوا كَمَا كُبِتَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ ۚ وَقَدْ أَنزَلْنَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ ۚ وَلِلْكَافِرِينَ عَذَابٌ مُّهِينٌ

ግልጾች ማስረጃዎችን ያወረድን ስንኾን እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩ፣ እነዚያ ከነሱ በፊት የነበሩት እንደተዋረዱ ይዋረዳሉ፤ ለካሃዲዎችም አዋራጅ ቅጣት አልላቸው።

يَوْمَ يَبْعَثُهُمُ اللَّهُ جَمِيعًا فَيُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوا ۚ أَحْصَاهُ اللَّهُ وَنَسُوهُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

አላህ ሁላቸውንም በሚቀሰቅሳቸው ቀን ይቀጣቸዋል፤ የሰሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል፤ የረሱት ሲሆኑ አላህ ዐውቆታል አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ ነው።

أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۖ مَا يَكُونُ مِن نَّجْوَىٰ ثَلَاثَةٍ إِلَّا هُوَ رَابِعُهُمْ وَلَا خَمْسَةٍ إِلَّا هُوَ سَادِسُهُمْ وَلَا أَدْنَىٰ مِن ذَ‌ٰلِكَ وَلَا أَكْثَرَ إِلَّا هُوَ مَعَهُمْ أَيْنَ مَا كَانُوا ۖ ثُمَّ يُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አላህ በሰማያት ውስጥ ያለውን፣ በምድርም ውስጥ ያለውን፣ ሁሉ የሚያውቅ መሆኑን አታይምን? ከሶስት ሰዎች መንሾካሾክ አይኖርም፣ እርሱ አራተኛቸው ቢሆን እንጂ፤ ከአምስትም አይኖርም፣ እርሱ ስድስተኛቸው ቢሆን እንጂ፤ ከዚያ ያነሰም የበዛም አይኖርም፣ እርሱ የትም ቢሆኑ አብሮዋቸው ቢሆን እንጂ፤ ከዚያም በትንሳኤ ቀን የሰሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል። አላህ ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነው።

أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ نُهُوا عَنِ النَّجْوَىٰ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا نُهُوا عَنْهُ وَيَتَنَاجَوْنَ بِالْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ وَمَعْصِيَتِ الرَّسُولِ وَإِذَا جَاءُوكَ حَيَّوْكَ بِمَا لَمْ يُحَيِّكَ بِهِ اللَّهُ وَيَقُولُونَ فِي أَنفُسِهِمْ لَوْلَا يُعَذِّبُنَا اللَّهُ بِمَا نَقُولُ ۚ حَسْبُهُمْ جَهَنَّمُ يَصْلَوْنَهَا ۖ فَبِئْسَ الْمَصِيرُ

ወደነዚያ በመጥፎ ከመሾካሾክ ወደ ተከለከሉት፣ ከዚያም ከርሱ ወደ ተከለከሉት ነገር ወደሚመለሱት በኃጢአትና ድንበርን በማለፍ መልክተኛውን በመቃወም ወደሚንሾካሸኩት አላየህምን? ሰላም ሊሉ በመጡህም ጊዜ አላህ በርሱ ባላናገረህ ቃል ያናግሩሃል። በነፍሶቻቸውም ውስጥ ነቢይ ከሆንክ በምንለው ነገር አላህ አይቀጣንም ኖሮዋልን? ይላሉ። ገሃነም የሚገቡዋት ሲሆኑ በቂያቸው ናት፤ ምን ትከፋም መመለሻ!

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا تَنَاجَيْتُمْ فَلَا تَتَنَاجَوْا بِالْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ وَمَعْصِيَتِ الرَّسُولِ وَتَنَاجَوْا بِالْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተንሾካሾችሁ ጊዜ በሃጢአትና ወሰንን በማለፉ መልክተኛውንም በመቃወም አትንሾካሾኩ፤ ግን በበጎ ስራና አላህን በመፍራት ተወያዩ፤ ያንንም ወደርሱ የምሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ

إِنَّمَا النَّجْوَىٰ مِنَ الشَّيْطَانِ لِيَحْزُنَ الَّذِينَ آمَنُوا وَلَيْسَ بِضَارِّهِمْ شَيْئًا إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ وَعَلَى اللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ الْمُؤْمِنُونَ

በመጥፎ መንሾኮሾክ ከሰይጣንን ብቻ ነው። እነዚያ ያመኑት ያዝኑ ዘንድ፣ ይቀሰቅሰዋል፤ በአላህ ፈቃድ ካልሆ በቀር በምንም አይጎዳቸውም፤ በአላህ ላይም አማኞች ይጠጉ።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا قِيلَ لَكُمْ تَفَسَّحُوا فِي الْمَجَالِسِ فَافْسَحُوا يَفْسَحِ اللَّهُ لَكُمْ ۖ وَإِذَا قِيلَ انشُزُوا فَانشُزُوا يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ

እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ለናንተ በመቀመጫዎች ስፍራ ተስፋፉ በተባላጩ ጊዜ፣ ስፍራን አስፉ፤ አላህ ያሰፋላችኋልና። ተነሱ በተባለም ጊዜ ተነሱ። አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም እውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል አላህም በምትሠሩት ሁሉ ወስጠ ዐዋቂ ነው።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نَاجَيْتُمُ الرَّسُولَ فَقَدِّمُوا بَيْنَ يَدَيْ نَجْوَاكُمْ صَدَقَةً ۚ ذَ‌ٰلِكَ خَيْرٌ لَّكُمْ وَأَطْهَرُ ۚ فَإِن لَّمْ تَجِدُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

እላንተ ያመናችሁ ሆይ! መልክተኛውን በተወያያችሁ ጊዜ ከመወየያታችሁ በፊት ምጽዋትን አስቀድሙ፤ ይህ ለናንተ መልካም ነው፤ አጥሪም ነው ባታገኙም አላህ መሐሪ አዛኝ ነው።

أَأَشْفَقْتُمْ أَن تُقَدِّمُوا بَيْنَ يَدَيْ نَجْوَاكُمْ صَدَقَاتٍ ۚ فَإِذْ لَمْ تَفْعَلُوا وَتَابَ اللَّهُ عَلَيْكُمْ فَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَأَطِيعُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ وَاللَّهُ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

ከውይይታችሁ በፊት ምጽዋቶችን ከማስቀደም ድህነትን ፈራችሁን? ባልሰራችሁም ጊዜ አላህ ከናንተ ጸጸትን የተቀበለ ሲሆን ሶላትን ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ፤ አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ፤ አላህም ውስጥ ዐዋቂ ነው።

 ۞ أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ تَوَلَّوْا قَوْمًا غَضِبَ اللَّهُ عَلَيْهِم مَّا هُم مِّنكُمْ وَلَا مِنْهُمْ وَيَحْلِفُونَ عَلَى الْكَذِبِ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ወደነዚያ አላህ በነርሱ ላይ የተቆጣባቸውን ሕዝቦች ወደ ተወዳጁት መናፍቃን፣ አላየኽምን? እነርሱ ከናንተ አይደሉም። ከነርሱም አይደሉም።እነሱም የሚያውቁ ሲኾኑ በውሸት ይምላሉ።

أَعَدَّ اللَّهُ لَهُمْ عَذَابًا شَدِيدًا ۖ إِنَّهُمْ سَاءَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

አላህ ለነርሱ ብርቱን ቅጣትን አዘጋጀ፤ እነሱ ይሰሩት የነበሩት ሥራ ምንኛ ከፋ!

اتَّخَذُوا أَيْمَانَهُمْ جُنَّةً فَصَدُّوا عَن سَبِيلِ اللَّهِ فَلَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ

መሐሎቻቸውን ጋሻ አድርገው ያዙ፤ ከአላህም መንገድ አገዱ፤ ስለዚህ ለነሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው።

لَّن تُغْنِيَ عَنْهُمْ أَمْوَالُهُمْ وَلَا أَوْلَادُهُم مِّنَ اللَّهِ شَيْئًا ۚ أُولَـٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ ቅጣት ምንንም ከነሱ አያድኗቸውም። እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው። እነርሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪ ናቸው።

يَوْمَ يَبْعَثُهُمُ اللَّهُ جَمِيعًا فَيَحْلِفُونَ لَهُ كَمَا يَحْلِفُونَ لَكُمْ ۖ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ عَلَىٰ شَيْءٍ ۚ أَلَا إِنَّهُمْ هُمُ الْكَاذِبُونَ

አላህ የተሰበሰቡ ኾነው በሚያስነሳቸው ቀን ለናንተ እንደሚምሉላችሁም እነሱ በሚጠቅም ነገር ላይ መኾናቸውን የሚያስቡ ኾነው ለርሱ በሚምሉበት ቀን አዋራጅ ቅጣት አላቸው፤ ንቁ እነሱ ውሸታሞቹ እነርሱ ናቸው።

اسْتَحْوَذَ عَلَيْهِمُ الشَّيْطَانُ فَأَنسَاهُمْ ذِكْرَ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ حِزْبُ الشَّيْطَانِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ الشَّيْطَانِ هُمُ الْخَاسِرُونَ

በነርሱ ላይ ሰይጣን ተሾመባቸው፤ አላህንም ማስታወስን አስረሳቸው፤ እነዚያ የሠይጣን ጭፍሮች ናቸው፤ ንቁ፤ የሰይጣን ጭፍሮች ከሳሪዎቹ እነርሱ ናቸው።

إِنَّ الَّذِينَ يُحَادُّونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ أُولَـٰئِكَ فِي الْأَذَلِّينَ

እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩት እነዚያ በጣም በወራዶቹ ውስጥ ናቸው።

كَتَبَ اللَّهُ لَأَغْلِبَنَّ أَنَا وَرُسُلِي ۚ إِنَّ اللَّهَ قَوِيٌّ عَزِيزٌ

አላህ ፦ እኔ በእርግጥ አሸንፋለሁ፤ መልክተኞቼም ያሸንፋሉ ሲል፤ ጽፏል። አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና።

لَّا تَجِدُ قَوْمًا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ يُوَادُّونَ مَنْ حَادَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَوْ كَانُوا آبَاءَهُمْ أَوْ أَبْنَاءَهُمْ أَوْ إِخْوَانَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ ۚ أُولَـٰئِكَ كَتَبَ فِي قُلُوبِهِمُ الْإِيمَانَ وَأَيَّدَهُم بِرُوحٍ مِّنْهُ ۖ وَيُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ ۚ أُولَـٰئِكَ حِزْبُ اللَّهِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ اللَّهِ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች፣ አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው ወይም ልጆቻቸው፤ ወይም ወንድሞቻቸው ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፤ እነዛ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል፤ ከርሱም በኾነ መንፈስ ደግፏቸዋል፤ ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባቸዋል፤ አላህ ከነርሱ ወዷል። ከርሱም ወደዋል፤ እነዚያ የአላህ ሕዝቦች ናቸው፤ ንቁ የአላህ ሕዝቦች እነሱ ምኞታቸውን የሚያገኙ ናቸው።

ቃሪዕ ይምረጡ