بِسْمِ اللّهِ الرَّحْمـَنِ الرَّحِيمِ


يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۖ لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

በሰማያት ውስጥ ያለው በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ ያሞግሳል፤ ንግሥናው የርሱ ብቻ ነው፤ ምስጋናም ለርሱ ነው፤ እርሱም በነገሩ ቻይ ነው።

هُوَ الَّذِي خَلَقَكُمْ فَمِنكُمْ كَافِرٌ وَمِنكُم مُّؤْمِنٌ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው፤ ከናንተም ከሐዲ አለ፤ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ተመልካች ነው።

خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ وَصَوَّرَكُمْ فَأَحْسَنَ صُوَرَكُمْ ۖ وَإِلَيْهِ الْمَصِيرُ

ሰማያትንና ምድርን በውነት ፈጠረ፤ ቀረፃችሁም ቅርፃችሁንም አሳመረ፤ መመለሻችሁም ወደርሱ ነው።

يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَيَعْلَمُ مَا تُسِرُّونَ وَمَا تُعْلِنُونَ ۚ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ

በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፤ የምትደብቁትንም የምትገልጡትንም ያውቃል አላህ በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው።

أَلَمْ يَأْتِكُمْ نَبَأُ الَّذِينَ كَفَرُوا مِن قَبْلُ فَذَاقُوا وَبَالَ أَمْرِهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

የነዚያ ከአሁን በፊት የካዱትና የክህደታችሁን ቅጣት ቅመሱ የተባሉት ሕዝቦች ወሬ አልመጣላችሁምን? ለነሱም አሳማሚ ቅጣት አልላቸው።

ذَ‌ٰلِكَ بِأَنَّهُ كَانَت تَّأْتِيهِمْ رُسُلُهُم بِالْبَيِّنَاتِ فَقَالُوا أَبَشَرٌ يَهْدُونَنَا فَكَفَرُوا وَتَوَلَّوا ۚ وَّاسْتَغْنَى اللَّهُ ۚ وَاللَّهُ غَنِيٌّ حَمِيدٌ

ይህቅጣትእርሱ መልክተኞቻቸው በአስረጂዎች ይመጡባችው ስለነበሩ ሰዎችም ይመሩልናልን? ስላሉና ስለካዱ ከእምነት ስለዞሩም ነው አላህም ከነሱ እምነት ተብቃቃ፤ አላህም ተብቃቂ ምስጉን ነው።

زَعَمَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَن لَّن يُبْعَثُوا ۚ قُلْ بَلَىٰ وَرَبِّي لَتُبْعَثُنَّ ثُمَّ لَتُنَبَّؤُنَّ بِمَا عَمِلْتُمْ ۚ وَذَ‌ٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ

እነዝያ የካዱት በፍፁም የማይቀሰቀሱ መሆናቸውን አስቡ፤ አይደለም በጌታዬ እምላለሁ፤ በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ፤ ከዝያም በሰራችሁት ሁሉ ትነገራላችሁ ይህም በአላህ ላይ ቀላል ነው፤ በላቸው።

فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَالنُّورِ الَّذِي أَنزَلْنَا ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ

በአላህና በመልክተኛውም በዚያም ባወረድነው ብርሃን እመኑ፤ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው በላቸው።

يَوْمَ يَجْمَعُكُمْ لِيَوْمِ الْجَمْعِ ۖ ذَ‌ٰلِكَ يَوْمُ التَّغَابُنِ ۗ وَمَن يُؤْمِن بِاللَّهِ وَيَعْمَلْ صَالِحًا يُكَفِّرْ عَنْهُ سَيِّئَاتِهِ وَيُدْخِلْهُ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَ‌ٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

ለመሰብሰቢያ ቀን የሚሰበስባችሁን ቀን አስታውሱ፤ይህ የመጎዳዳኢቶቹን ይሰረይለታል፤ ይፍቅለታል ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች፣ በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያገባዋል፤ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው።

وَالَّذِينَ كَفَرُوا وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا أُولَـٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ خَالِدِينَ فِيهَا ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ

እነዚያም የካዱና በአንቀጾቻችን ያስተባበሉ እነዚያ በውስጡ ዘውታሪዎች ሲሆኑ የ እሳት ጓዶች ናቸው፤ መመለሻቸውም ከፋ!

مَا أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ وَمَن يُؤْمِن بِاللَّهِ يَهْدِ قَلْبَهُ ۚ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

ከመከራም ማንንም አይነካም በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ፤ በአላህም የሚያምን ሰው ልቡን ለት ዕግሥት ይመራዋል፤ አላህም ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነው።

وَأَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ ۚ فَإِن تَوَلَّيْتُمْ فَإِنَّمَا عَلَىٰ رَسُولِنَا الْبَلَاغُ الْمُبِينُ

አላህን ተገዙ፤ መልክተኛውንም ታዘዙ፤ ብትዞሩም መልክተኛውን አይጎዱም፤ በመልክተኛውም ላይ ማድረስ ያለበት ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው።

اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ وَعَلَى اللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ الْمُؤْمِنُونَ

አላህ ከርሱ በቀር አምላክ የለም፤ በአላህም ላይ አማኞቹ ይመኩ።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ مِنْ أَزْوَاجِكُمْ وَأَوْلَادِكُمْ عَدُوًّا لَّكُمْ فَاحْذَرُوهُمْ ۚ وَإِن تَعْفُوا وَتَصْفَحُوا وَتَغْفِرُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሚስቶቻችሁና ከልጆቻችሁ ከአላህ መንገድ በማስተካከል ለናንተ ጠላቶች የኾኑ አልሉ፤ ስለዚህ ተጠንቀቋቸው፤ ይቅርታ ብታደርጉ ብታልፏቸውም ብትምሯቸውም አላህ በጣም መሐሪ አዛኝ ነው።

إِنَّمَا أَمْوَالُكُمْ وَأَوْلَادُكُمْ فِتْنَةٌ ۚ وَاللَّهُ عِندَهُ أَجْرٌ عَظِيمٌ

ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለናንተ መፈተኛ ብቻ ናቸው፤ አላህም እርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አለ።

فَاتَّقُوا اللَّهَ مَا اسْتَطَعْتُمْ وَاسْمَعُوا وَأَطِيعُوا وَأَنفِقُوا خَيْرًا لِّأَنفُسِكُمْ ۗ وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفْسِهِ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

አላህን የቻላችሁትን ያክል ፍሩት፤ ትእዛዙን ስሙም፤ ታዘዙም፤ ለግሱም፤ነፍሶቻችሁ መልካምን ይሰጣችኋልና፤ የነፍሱንም ንፍገት የሚጠብቅ ሰው እነዚያ እነሱ ፍላጎታቸውን የሚያገኙት ናቸው።

إِن تُقْرِضُوا اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا يُضَاعِفْهُ لَكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ۚ وَاللَّهُ شَكُورٌ حَلِيمٌ

ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩ ምንዳውን ለናንተ ይደራርበዋል፤ ለናንተም ይምራል፤ አላህ አመስጋኝ ታጋሽ ነው።

عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

ሩቁን ሚስጢር ግልጹንም ሁሉ ዐዋቂው አሸናፊው ጥበበኛው ነው።

ቃሪዕ ይምረጡ